Fana: At a Speed of Life!

የኮሪደር ልማቱ የኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ዘርፍ እንዲነቃቃ ጉልህ ፋይዳ እያበረከተ ነው – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሪደር ልማቱ በተለይም የኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ዘርፍ እንዲነቃቃ ጉልህ ፋይዳ እያበረከተ መሆኑን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተናገሩ።

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት ፥ የኮሪደር ልማት ኢንሼቲቩ ሀገራችንን ብሎም ሀረር ከተማን በብዙ መልኩ እየቀየረ የሚገኝ ዘመን ተሻጋሪ ፕሮጀክት ነው።

በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችም የክልሉን የወደፊት ዕድገት ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የኮሪደር ልማቱ በተለይም የኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ዘርፍ እንዲነቃቃ ጉልህ ፋይዳ እያበረከተ መሆኑን ገልጸው ፤ የሥራ ባህልን በመቀየርና ወጪን በመቀነስ ረገድም እያገዘ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።

የኮሪደር ልማቱ ስኬት መሳካት የክልሉ መንግስት ግብረ-ሃይል በማቋቋም የተጠናከረ ድጋፍና ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎችም የዜጎችን የልማት ተሳትፎ እንዲነቃቃ እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡

አቶ ኦድሪን በምልከታቸው በኮሪደር ልማት ስራው እየተሳተፉ የሚገኙ ዜጎችን አበረታተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.