Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮያ ልዑክ በግሎባል ሉዓላዊ የዕዳ ድርድር መድረክ ላይ ተሳተፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑክ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ባዘጋጀው የግሎባል ሉዓላዊ የዕዳ ድርድር መድረክ ላይ ተሳተፈ፡፡

የ ‘አይ ኤም ኤፍ’ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጂኦርጄቫ፣ የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጄይ ባንጋ እና የቡድን-20 የወቅቱ ሊቀ-መንበር የብራዚል ገንዘብ ሚኒስትር ፈርናንዶ ሀዳድ መድረኩን መርተውታል፡፡

በዚሁ መድረክ ላይ የተሳተፉት የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)÷  የእዳ ሽግሽግን በተመለከተ ኢትዮጵያ ያላትን ተሞክሮ አጋርተዋል፡፡

ሀገራት ዕዳቸውን ለመክፈል የሚያደርጓቸው በጎ ጥረቶች እየታዩ በፍጥነት ጊዜያዊ የዕዳ ክፍያ እፎይታ ሊደረግላቸው እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡

የ ‘አይ ኤም ኤፍ’ ፕሮግራሞች በቦርድ ከፀደቁ ጊዜ ጀምሮ ባሉት ሥድስት ወራት ውስጥ የዕዳ ማሸጋሸግ ሂደቱ የሚጠናቀቅበት አሠራር ተግባራዊ ማድረግ የሚያስቸል አዲስ ሐሳብም አቅርበዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም የዕዳ ሽግሽግ ሂደት ውጤታማነት፣ ተገማችነት እና የጊዜ ሰሌዳ አስፈላጊነት ላይ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.