Fana: At a Speed of Life!

የአትሌት መዲና የ5 ሺህ ሜትር ውጤት በክብረ-ወሰንነት ፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) – በኢትዮጵያዊቷ አትሌት መዲና ኢሳ ከ20 ዓመት በታች የ5000 ሜትር የሴቶች የሩጫ ውድድር የተመዘገበው ውጤት በክብረ-ወሰንነት ፀደቀ፡፡

ባለፈው ወር በቤልጂየም ብራስልስ በተካሄደው ሩጫ የ19 ዓመቷ አትሌት መዲና በ14 ደቂቃ ከ21 ሰከንድ 89 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሩን ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡

በአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ከ20 ዓመት በፊት የተመዘገበው 14 ደቂቃ 30 ሰከንድ 88 ማይክሮ ሰከንድ የውድድሩ ክብረ-ወሰን ነበር፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.