ኢትዮጵያ በአንካራ የተፈፀመውን የሽብር ጥቃት አወገዘች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በቱርክ አንካራ ከተማ የተፈፀመውን የሽብር ጥቃት እንደምታወግዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ÷ ኢትዮጵያ በቱርክ አንካራ በሚገኘው የቱርክ ኤርስፔስ ኢንዱትስትሪ ላይ በተፈፀመው የሽብር ጥቃት ምክንያት በሞቱ ሰዎች ማዘኗን ገልጾ፤ በጥቃቱ ሰለባ ለሆኑ የሟች ቤተሰቦች፣ ለቱርክ ህዝብ እና መንግስት መፅናናትን ተመኝቷል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የተፈፀመውን የሽብር ጥቃት ያወግዛል ያለው መግለጫው፤ ቱርክ አሸባሪዎችን ለመዋጋት በምታደርገው ጥረት የኢትዮጵያ መንግስት ከጎኗ እንደሚቆም አረጋግጧል፡፡