Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ በ2028 ለአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት 1 ነጥብ 3 ትሪሊየን ብር አስተዋጽዖ ያደርጋል ተባለ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ በፈረንጆቹ 2028 ለአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት 1 ነጥብ 3 ትሪሊየን ብር አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ ጂ.ኤስ.ኤም.ኤ የተሰኘ ዓለም አቀፍ ድርጅት አመላከተ።

ኢትዮ ቴሌኮም እና ግዙፍ ዓለም አቀፍ የሞባይል ኦፕሬተሮች እና መለስተኛ ኦፕሬተሮችን ጨምሮ 26 የቦርድ አባላት ያሉት ዓለም አቀፉ ጂ.ኤስ.ኤም.ኤ በጋራ በመሆን የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚን በተመለከተ የፓናል ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡

በውይይቱ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩንና “የጂ.ኤስ.ኤም.ኤ” ዓለም አቀፍ ሬጉላቶሪ ኦፊሰር ጆን ጊዩስቲ ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በመድረኩ የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን ያለመው የኢትዮጵያ ዲጂታላይዜሽን የመጀመሪያው አጠቃላይ ሪፖርት ይፋ ሆኗል።

በኢትዮጵያ የቴሌኮም ማሻሻያ እና የሞባይል ቴክኖሎጂ ኢንቨስትመንቶች በግብርና፣ በአምራች ዘርፍ፣ በሕዝብ አገልግሎትና በሌሎች ዘርፎች ፈጣን እድገት እያመጡ እንደሚገኙ በመድረኩ ተገልጿል፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ በፈረንጆቹ 2028 ለአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት 1 ነጥብ 3 ትሪሊየን ብር አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ ተመላክቷል፡፡

ከ1 ሚሊየን በላይ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን እንደሚፈጥርና ለመንግሥት ተጨማሪ 57 ቢሊየን ብር ከታክስ ገቢ እንደሚያስገኝም በሪፖርቱ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.