Fana: At a Speed of Life!

አቡበከር ናስር ሱፐር ስፖርት ዩናትድን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማሜሎዲ ሰንዳውንስ ሲጫዎት የነበረው አቡበከር ናስር ሌላኛውን የደቡብ አፍሪካ ክለብ ሱፐር ስፖርት ዩናይትድን ተቀላቅሏል፡፡

የፊት መስመር አጥቂው በማሜሎዲ ሰንዳውንስ ቆታው ባጋጠመው ከበድ ያለ ጉዳት ምክንያት በክለቡ ያልተሳካ ገዜ መሳላፉ የሚታወስ ነው፡፡

አቡበከር በሰንዳውንስ አለመፈለጉን ተከትሎ ሱፐር ስፖርት ዩናይትድን ለመቀላቀል ንግግር ሲደርግ የቆየ ሲሆን በአንድ ዓመት ኮንትራት በሱፐርስፖርት ዩናይትድ ለመቆየት ስምምነት ላይ መድረሱን ክለቡ አስታውቋል፡፡

የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ አቡበከር ናስር በ2009 የውድድር ዘመን ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጋር መተዋወቅ የቻለ ሲሆን በኢትዮጵያ ቡና እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ድንቅ ጊዜን ማሳለፍ ችሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.