Fana: At a Speed of Life!

ቱርክ በኩርድ ታጣቂ ቡድን ይዞታዎች ላይ ጥቃት መፈፀሟን ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ቱርክ ትናንት ምሽት የተፈፀመውን የአንካራ ከተማ ጥቃት አቀናብሯል ባለችው የኩርድ ታጣቂ ቡድን (ፒኬኬ) ይዞታዎች ላይ ጥቃት መፈፀሟን አስታውቃለች፡፡

የቱርክ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው÷ በፒኬኬ ላይ በተወሰደው የአፀፋ ጥቃት በኢራቅ እና ሶሪያ በሚገኙ 32 የቡድኑ ይዞታዎችን ማውደም ተችሏል፡፡

በአንካራ የደረሰውን ጥቃት ቡድኑ እንደፈፀመ የገለፀው ሚኒስቴሩ፤ ጥቃቱን የፈጸሙ የቡድኑ ታጣቂዎች የቱርክ የፀጥታ ሀይሎች በወሰዱት እርምጃ መገደላቸውን አስታውቋል፡፡

የቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን በጥቃቱ ወቅት የፀጥታ ሀይሎች በፍጥነት ወደ ቦታው በመድረስ የሽብር ጥቃቱን ማስቆማቸውን ገልፀው፤ የአሸባሪዎች ህልም አይካም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በአንካራ ከተማ በሚገኘው የቱርክ ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪ ላይ በተፈፀመ የሽብር ጥቃት አምስት ሰዎች ሲሞቱ ከ22 ሰዎች በላይ ደግሞ ቆስለዋል፡፡

ከአንካራው ጥቃት በስተጀርባ እጁ እንዳለበት የተገለፀው የኩርድ ሰራተኞች ፓርቲ ፒኬኬ ከፈረንጆቹ 1980 ጀምሮ ለኩርድ ነፃነት የሚታገል ቡድን ሲሆን በቱርክ፣ አሜሪካ እና እንግሊዝ በአሸባሪነት መፈረጁ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.