Fana: At a Speed of Life!

ድሬዳዋ አስተዳደር የመጀመሪያ ሩብ አመት ስራዎች በዕቅድ መሰረት መከናወናቸውን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በተያዘው እቅድ መሰረት የመጀመሪያ ሩብ አመት ስራዎች መከናወናቸው ተገለፀ፡፡

የ2017 በጀት አመት የድሬዳዋ አስተዳደር አስፈፃሚ ተቋማት የመጀመሪያው ሩብ የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቧል፡፡

በሪፖርቱ የአስተዳደሩ መንግስት የማስፈፀም አቅም በማጎልበት የዜጎችን እርካታ ወደ ላቀ ደረጃ የማሸጋገር ተደማሪ ውጤት ለማምጣት የተያዙ ዕቅዶች በተገቢው እየተከናወኑ እንደሆነ ተገልጿል።

የበጀት ዓመቱ የዝግጅት ምዕራፍ እና የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች በትኩረት እንዲከናወኑ ከማድረግ ባሻገር አበይት ተግባራት መከናወናቸው በሪፖርቱ መገለፁን የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የአስተዳደሩ ዋነኛ የትኩረት መስኮች ከተረጂነት የመላቀቅ፣ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ እና ምርትና ምርታማነትን የማሳደግ እንደሆነ ተገልጿል።

እንዲሁም የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነት የሚያስከትለውን ጫና መቀነስና ማረጋጋት፣ የስራ እድል ፈጠራ እንዲኖር ማስቻል፣ የኮሪደር ልማት ስራዎችን በቅንጅትና በፍጥነት የማከናወንና ምቹና ዘመናዊ ከተማ ማድረግ የአስተዳደሩ የበጀት ዓመቱ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑ ተመላክቷል።

የአምራች ዘርፍን የማምረት አቅም በማሳደግ ተጨማሪ የስራ እድል እንዲፈጥር የማድረግ፣ የትምህርት እና ጤና ተደራሽነትና ጥራትን የማረጋገጥ፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር የሚያሳልጡ የመንገድ ግንባታዎችና የንፁህ መጠጥ ውሀ ተደራሽነት፣ የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ስራዎችን መስራትም የዕቅዱ ትኩረት መሆኑ ተጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.