Fana: At a Speed of Life!

የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኤርትራ ጋር ጥቅምት 21 እና 24 ቀን 2017 ዓ.ም ለሚያደርገው የቻን ማጣሪያ ደርሶ መልስ ጨዋታ ለ23 ተጨዋቾች ጥሪ ቀረበ፡፡

የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ባቀረቡት ጥሪ መሠረት÷ በግብ ጠባቂ ዘርፍ ሰኢድ ሀብታሙ፣ በረከት አማረ እና ዳግም ተፈራ ተካትተዋል፡፡

አስራት ቱንጆ፣ ሱሌማን ሀሚድ፣ ያሬድ ባዬ፣ ወልደ አማኑኤል ጌቱ፣ ፍሬዘር ካሳ፣ ራምኬል ጀምስ፣ ደስታ ደሙ እና ረመዳን የሱፍ ደግሞ ለተከላካይ ሥፍራ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡

እንዲሁም ለአማካይ ሥፍራ ተጫዋችነት ጋቶች ፓኖም፣ በረከት ወልዴ፣ አብዱልከሪም ወርቁ፣ አብነት ደምሴ፣ እንዳልካቸው መስፍን እና ቢኒያም አይተን ጥሪ እንደተደረገላቸው ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል መሐመድኑር ናስር፣ ኪቲካ ጅማ፣ ፋሲል አስማማው፣ በረከት ደስታ፣ አማኑኤል ኤርቦ እና ቸርነት ጉግሳ ለአጥቂነት ጥሪ ቀርቦላቸዋል መባሉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬስን መረጃ አመላክቷል፡፡

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾችም ነገ በጁፒተር ሆቴል ሪፖርት በማድረግ ዝግጅት እንዲጀምሩ አሰልጣኙ አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.