Fana: At a Speed of Life!

ፖርቹጋል ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርት ዘርፍ በትብብር መስራት እንደምትፈልግ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከፖርቹጋል የውጭ ጉዳይና የትብብር ሚኒስትር ኑኖ ሳምፓዮ ጋር ተወያየይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያና በፖርቹጋል መካከል በትምህርት ዘርፍ ያለው ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና በሌሎችም ዘርፎች የአካዳሚክ ትብብሮች በሚጠናከሩበትና አሁን ያለው ግንኙነትን በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውም ተጠቁሟል፡፡

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)÷ሚኒስቴሩ የትምህርት ሙዚዬም እያቋቋመ በመሆኑ ፖርቹጋል በኢትዮጵያ የትምህርት ታሪክ ውስጥ የነበራትን ተሳትፎና ታሪክ ልታኖር እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

ኑኖ ሳምፓዮ በበኩላቸው÷ፖርቹጋል ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርትና በሌሎችም መስኮች ያላትን የትብብርና የወዳጅነት ግንኙነት አጠናክሮ የማስቀጠል ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል፡፡

በትምህርትና በባህል ዘርፍ ያለውን ወዳጅነትና የትብብር ግንኙነት በማስፋት ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ነጻ የትምህርት እድል የማሳደግ ፍላጎት እንዳላትም ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የፖርቹጋል አምባሳደር ሉዊዛ ፋራጋሶ ÷ የፖርቹጋል ብሄራዊ ቀንን ምክንያት በማድድግ በያሬድ የመዚቃ ትምህርት ቤት የባህል ትርኢት የማቅረብ ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.