አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኢሉ አባ ቦር ዞን የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በኢሉ አባ ቦር ዞን የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡
በጉብኝት መርሐ ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች እና የዞን አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት በጉብኝታቸው በዳሪሙ ወረዳ በክላስተር እየለማ የሚገኘውን የሩዝ ማሳ መመልከታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ አቶ ሽመልስ በቡኖ በደሌ ዞን ዳቦ ሃና ወረዳ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡