Fana: At a Speed of Life!

ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ271 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሶስት ወራት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ271 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ መሰብሰቡን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ ቤት አስታውቋል።

በጽ/ቤቱ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን ዳንኤል እንዳሉት፥ በ2017 በጀት ዓመት ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ድጋፍ ለመሰብሰብ ታቅዷል፡፡

በሩብ ዓመቱም በሀገር ውስጥና በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በቦንድ ሽያጭ፣ በ8100 አጭር የጽሑፍ መልዕክትና በስጦታ ከ271 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ መሰብሰቡን ተናግረዋል።

በበጅት ዓመቱ የታቀደውን ድጋፍ ለማሰባሰብ በትኩረት ይሰራል ያሉት ስራ አስፈጻሚው፥ ሕዝቡም እስከ ግንባታው ፍጻሜ ድጋፉን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

መገናኛ ብዙሃንና የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች የገቢ ማሰባሰቢያ አማራጮችን ለሕብረተሰቡ በማሳወቅ ሚናቸውን እንዲወጡ መጠየቃቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.