Fana: At a Speed of Life!

የጃፓን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ቱሪዝም ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፓን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ቱሪዝም ኢንቨስትመንትና ሌሎች የቢዝነስ አማራጮች ላይ እንዲሰማሩ በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዳባ ደበሌ ጥሪ አቀረቡ፡፡

በጃፓን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አዘጋጅነት የኢትዮጵያ የቱሪስት መስህቦችን የሚያስተዋውቅ የቱሪዝም መድረክ ተካሄዷል።

በወቅቱ ስለ ኢትዮጵያ የቱሪዝም ሀብት እና የቱሪዝም መዳረሻዎች ገለጻ ያደረጉት አምባሳደር ዳባ ደበሌ÷ ጃፓናዊያን በኢትዮጵያ የቱሪዝም እና ሌሎች የኢንቨስትመንትና እና የቢዝነስ አማራጮች ላይ እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቸኛው አፍሪካን ከጃፓን በቀጥታ የሚያገናኝ አየር መንገድ መሆኑን በመጥቀስ፤ ጃፓናዊያን ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራትን ለመጎብኘት መልካም አጋጣሚ መሆኑንም ተናግረዋል።

በመድረኩ አምባሳዳሮችና ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.