Fana: At a Speed of Life!

ምርጫ ቦርድ 11 ፓርቲዎችን ለጊዜው አገደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጠቅላላ ጉባዔ፣ በኦዲት እና በሴት አባላት አማካኝነት ከሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ጋር በተያያዘ 11 የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማገዱን ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አሳወቀ፡፡

ፓርቲዎቹም÷የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ፣ አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የጌዲኦ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የሐረሪ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የገዳ ሥርዓት ለኦሮሞ ነጻነት ፓርቲ፣ የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ የጋምቤላ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ኅብረት እና አገው ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ናቸው፡፡

በፓርቲዎቹ ላይ የተሰጠው የዕግድ ውሳኔም ቦርዱ የተለየ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ለጊዜው ከማንኛውም ሕጋዊ እንቅስቃሴ ታቅበው እንዲቆዩ የሚያደርግ ነው፡፡

የዕግድ ውሳኔውን ቦርዱ እስከሚያነሳ ድረስም ከላይ የተገለጹት ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱ በሚያዘጋጃቸው ጉባዔዎች ላይ ሊገኙ፣ ሊመርጡም ሆነ ሊመረጡ እንዲሁም በኮሚቴ አባልነት ሊያገለግሉ አይችሉም ተብሏል፡፡

የጋራ ምክር ቤቱ የዕግድ ውሳኔ የተላለፈባቸውን ፓርቲዎች ከማንኛውም የምክር ቤቱ ሥራዎች እና እንቅስቃሴዎች እንዳይካፈሉ እንዲያደረግ ቦርዱ አሳስቧል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.