Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ከአንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2017፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መካከል ያለውን ቀጣናዊ የሰላም እና የጸጥታ ጉዳዮች ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በዚህም የባለብዙ ወገን ትብብርን በይበልጥ ማጠናከርና ማሳደግ እንደሚገባ መምከራቸውን ፕሬዚዳንቱ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

ትናንት የተካሄደው የአፍሪካ እና የተመድ የጋራ ጉባዔም የተሳካ እንዲሆን ዋና ጸሐፊው ላበረከቱት አስተዋፅዖ ፕሬዚዳንቱ አመስግነዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.