Fana: At a Speed of Life!

በማንዱራ ወረዳ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሃይሎች ወደ ሰላም መምጣታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሃይሎች ለሰላም ቅድሚ በመስጠት ወደ ወረዳ ማዕከል ገብተዋል።

ለሰላም ተመላሾቹ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ም/አፈ-ጉባዔ መለሰ ኪዊ፣ የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱ እና የሃገር ሽማግሌዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል ።

በወረዳው ሠላም እንዲሰፍንና የልማት ሥራዎች እንዲፋጠኑ የፀጥታ አካላትና የሃገር ሽማግሌዎች ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና መቅረቡን የወረዳው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.