Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና የኦስትሪያ የቢዝነስ ፎረም ነገ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና የኦስትሪያ ቢዝነስ ፎረም ነገ እንደሚካሄድ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር)÷ በፎረሙ የሁለቱ ሀገራት ግዙፍ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉና አጋጣሚው የሀገራቱን የኢኮኖሚ ትብብር ይበልጥ እንደሚያጠናክር ተናግረዋል፡፡

የኦስትሪያ ኩባንያዎች እና ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማየት እንደሚመጡም ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ የኦስትሪያ አምባሳደር ሲሞን ናፕ (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷በቢዝነስ ፎረሙ በጤና እንዲሁም በአምራች ዘርፉ የተሰማሩ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉ ተናግረዋል።

የፎረሙ መካሄድ የጋራ ልምድን ከመቀመርና ትስስርን ከማጠናከር ባለፈ የሁለቱን ሀገራት ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የላቀ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል።

የቢዝነስ ፎረሙን በኢትዮጵያ የኦስትሪያ ኤምባሲ እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በትብብር ያዘጋጁት መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.