Fana: At a Speed of Life!

በሰፊ መዳረሻ የላቀ አገልግሎት ለመስጠት እየሠራሁ ነው- የኢትዮጵያ አየር መንገድ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በተቀላጠፈ እና በሰፊ መዳረሻ የላቀ አገልግሎት ለመስጠት እየሠሩ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው አስታወቁ፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው የአየር መንገዱን የካርጎ ሎጅስቲክስ አገልግሎት በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ÷ አየር መንገዱ የካርጎ ጭነት አገልግሎት የሚሰጡ 16 ግዙፍና መካከለኛ አውሮፕላኖች እንዳሉት አንስተዋል፡፡

በቀጣይም ተቋሙ በተቀላጠፈና በሰፊ መዳረሻ የላቀ አገልግሎት ለመስጠት እየሠራ መሆኑን ገልጸው÷ አሁን ላይ በ140 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች የተለያዩ የጭነት አገልግሎቶችን እያጓጓዘ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በ2016 በጀት ዓመት ከ758 ሺህ ቶን በላይ ጭነት መጓጓዙን እና ከአጠቃላይ የአየር መንገዱ ገቢም የካርጎ ዘርፍ 1 ነጥብ 65 ቢሊየን ዶላር መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡

በ2017 በጀት ዓመትም አየር መንገዱ የካርጎ ሎጅስቲክስ ዘርፉን ከ10 በመቶ በላይ ለማሳደግ እየሠራ ነው ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.