በመንግስት ሰራተኞች አዲሱ የደመዎዝ ጭማሪ አፈጻጸም መመሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የመንግስት ሰራተኞች አዲሱ የደመዎዝ ጭማሪ አፈጻጸም መመሪያ ላይ ከክልልና ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊዎች ጋር ተወያይቷል፡፡
በውይይት መድረኩ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ሃይሌ (ዶ/ር)፣ የክልልና ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ የመንግስት ሠራተኞች አዲሱ ደመዎዝ ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡