Fana: At a Speed of Life!

የግብርና እና የገጠር ልማት ፖሊሲው ግብርና የኢኮኖሚ ዕድገት መሪ እንዲሆን አስችሏል-ግርማ አመንቴ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ የግብርና እና ገጠር ልማት ፖሊሲ ግብርና የኢኮኖሚ ዕድገት የመሪነት ሚናውን እንዲወጣ አስችሏል ሲሉ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ገለጹ።

ሀገር አቀፍ የግብርና እና ገጠር ልማት ፖሊሲ ማስተዋወቂያ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

ግርማ አመንቴ በዚህ ወቅት÷ ፖሊሲው ምርታማነትን በማሳደግ፣ ድህነትን በመቀነስና የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ግብርና የኢኮኖሚ ዕድገት የመሪነት ሚናውን እንዲወጣ ማስቻሉን ገልጸዋል፡፡

አዲሱ የግብርና ገጠር ልማት ፖሊሲ የተቀረጸው ተግዳሮቶችን በመቅረፍ የግብርና ዘርፉን ከሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች ጋር የበለጠ ለማስተሳሰር፣ የተፈጥሮ ሀብትን በዘላቂነት ለመጠበቅ እና የግብርናን ምርታማነትና ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ እንደሆነም አንስተዋል፡፡

ከ1994ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ የነበረው የገጠር ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ በአዲሱ የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ የተተካው ባሳለፍነው ዓመት በህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት በመፅደቁ ነው።

የፖሊሲው አላማ በ2030 ዓ.ም ግብርናን በማሻገር በገጠር መዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት እንደሆነ ተመላክቷል፡፡

በፍቅርተ ከበደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.