Fana: At a Speed of Life!

ተቋማቱ ለቢሾፍቱ ከተማ የኮሪደር ልማት ከ40 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያለው ቁሳስ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ለቢሾፍቱ ከተማ አሥተዳደር የኮሪደር ልማት ማስፈጸሚያ ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የግንባታ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፉን የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ እና የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ለከተማ አሥተዳደሩ አስረክበዋል።

በዚሁ ወቅት ሚኒስትሯ ባደረጉት ንግግር÷ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የኮሪደር ልማት የከተሞችን ብሎም የኢትዮጵያን ገጽታ የሚቀይር ነው ብለዋል፡፡

ለከተማ አሥተዳደሩ የተደረገው ድጋፍ በከተማዋ የተጀመረውን ልማት ለማፋጠን ያግዛል ማለታቸውን የጉሙሩክ ኮሚሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ኮሚሽነር ደበሌ በበኩላቸው÷ የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን ጸጋዎች በአግባቡ ለመጠቀም ዕድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.