ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሜዳ ቴኒስ የታዳጊ ወንዶች ጥንድ ውድድር ጃፓንና ሕንድን አሸንፋ ወርቅ አገኘች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፍ የሜዳ ቴኒስ የታዳጊ ወንዶች ጥንድ ውድድር ኢትዮጵያ ጃፓን እና ሕንድን በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች፡፡
ይህ ውድድር በዘርፉ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘችበት መሆኑም ተገልጿል፡፡
በውድድሩም ዳዊት ሸለመ እና ዳዊት ፍስሐ 64/25 እና 10/5 በሆነ ውጤት ማሸነፋቸውን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
የፍጻሜ ውድድሩ የተካሄደው በአዲስ አበባ ቴኒስ ክበብ መሆኑም ተገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ላለፉት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ ጠረጴዛ ቴኒስ ውድድር በስኬት ዛሬ መጠናቀቁን የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
ከውድድሩ ቅድመ ዝግጅት እስከ ማጠናቀቂያ ምዕራፍ ድረስ አስፈላጊውን ተሳትፎና ትብብር ላደረጉ አካላት ምሥጋና አቅርበዋል፡፡