ማንቼስተር ዩናይትድ እና ቶተንሀም ሆትስፐር ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም ሆትስፐር ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡
በኦልድትራፎርድ ብረንትፎርድን ያስተናገደው የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ቡድን ማንቼስተር ዩናይትድ ብረንትፎርድን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
በጨዋታው ብረንትፎርድ በኢታን ፒንኖክ ግብ ቀዳሚ ቢሆንም ከእረፍት መልስ አሊያንድሮ ጋርናቾ እና ራሰመስ ሆይለንድ ባስቆጠሯቸው ግቦች ማንቼስተር ዩናይትድ 2 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል፡፡
አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ ቶተንሃም ሆትስፐር ዌስትሃም ዩናይትድን 4 ለ 1 አሸንፏል፡፡
ዲያን ኩልሴቭስኪ፣ ይቬስ ቢሱማ፣ ሰን ሁዊንግ ሚን እና አሪዎላ (በራሱ መረብ ላይ) ሲያስቆጥሩ የዌስትሃም ዩናይትድን ብቸኛ ጎል ሞሀመድ ኩዱስ አስቆጥሯል፡፡
በሌሎቸች ጨወታዎች አስቶንቪላ ፉልሃምን 3 ለ 1፣ ብራይተን ኒውካስልን 1 ለ 0፣አቬርተን ኢፕስዊችን 2 ለ 0፣ ሌስተር ሲቲ ሳውዝሃምፐተንን 3 ለ 2 አሸንፈዋል።