ወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎቹን አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 224 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ከተመራቂዎቹ ውስጥም 25 ነጥብ 5 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው ተብሏል።
በምረቃ መርሃ ግብሩም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አወል ሰይድ(ዶ/ር)፣የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባል እና የኮምቦልቻ ቻ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ ሙስጠፋ ጀማል እና የትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ ከበደ ግዛው(ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች ተገኝተዋል።
በዚህ ወቅት አወል ሰይድ (ዶ/ር) ÷ለተመራቂ ተማሪዎች ለማደግ አቋራጭ መንገድ የለምና ሁልጊዜም እራሳችሁን ማሳደግና ማስተማር ላይ አተኩሩ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዩኒቨርሲቲው በ38 ቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ተማሪዎቹን እያስተማረ ሲሆን÷ አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ በተቋሙ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ችግር ፈቺ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ወሎ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ሰዓት ከ21 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል።
በእለኒ ተሰማ