ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) የማክሮ ኢኮኖሚ እድገት እና ቁልፍ የክዋኔ መስፈሪያዎች የቀረቡበትን የካቢኔ የ100 ቀን የአፈፃፀም ግምገማ አስጀመሩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤትን በመሰብሰብ የማክሮ ኢኮኖሚ እድገት እና ቁልፍ የክዋኔ መስፈሪያዎች የቀረቡበትን የካቢኔ የ100 ቀን የአፈፃፀም ግምገማ አስጀምረዋል።
ግምገማው ዓለም አቀፋዊ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዝንባሌዎችን እና ፍኖቶችን በመፈተሽ በኢትዮጵያ ላይ የሚኖራቸውን ተፅዕኖ መመልከቱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
8 ነጥብ 45 በመቶ በተተነበየው የመጪው ዓመት እድገት የለውጡ አበረታች ውጤቶች አካታች እና ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትን የሚያሳዩ፣ የጨመረ የመንግሥት ገቢ እና ኢንቨስትመንት ያስገኙ፣ የመንግሥት ዕዳን የቀነሱ፣ በመንግሥት ይዞታ ስር ያሉ ተቋማትን ተወዳዳሪነት የጨመሩ፣ የውጭ ምንዛሪ ያስገኙ፣ የበለጠ ተወዳዳሪነትን የታየበት የፋይናንስ ዘርፍ ያመጡ፣ ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢን የፈጠሩ ብሎም የዘርፍ ምርታማነትን ያሳደጉ መሆናቸው ተነስቷል፡፡
የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት በተለይም እንደ ማኑፋክቸሪንግ እና ኮንስትራክሽን ባሉ ዘርፎች የተፋጠነ እንደሚሆን ይጠበቃል ተብሏል።