Fana: At a Speed of Life!

የዓለም አስተዳደራዊ መዋቅር ለታዳጊ ኢኮኖሚ ምላሽ ሰጪ እንዲሆን በንቃት መስራት አለብን – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሪክስ አባል ሀገራት የዓለም አስተዳደራዊ መዋቅር ለታዳጊ ኢኮኖሚ ምላሽ ሰጪ እንዲሆን በንቃት መስራት አለብን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሞስኮ እየተካሄደ ባለው የብሪክስ ቢዝነስ ፎረም ላይ በዙም ባደረጉት ንግግር ባስተላለፉት መልዕክት፤ የብሪክስ አባል ሀገራት የዓለምን 50 በመቶ ህዝብ እንደሚወክሉ ገልጸዋል።

በመሆኑም ይህ ትልቅ አቅም በዓለም የኢኮኖሚ ዕድገትና ዘላቂ ልማት ላይ ተጨባጭ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

ይህንን አቅም ወደ ተግባር ለመለወጥም በንቃት መስራት ይገባናል ብለዋል።

በዚህም የዓለም አስተዳደራዊ መዋቅር ወካይ፣ አካታችና ለታዳጊ ኢኮኖሚ ምላሽ ሰጪ እንዲሆን ለማስቻል በንቃት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.