ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትን ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትን እንቅስቃሴዎች ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት አጠናክራ እንደምትቀጥል አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ገለፁ፡፡
በአፍሪካ ሕብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የኢፌዴሪ ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ሂሩት ዘመነ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማሃማት አቅርበዋል።
በወቅቱ ባደረጉት ውይይትም እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ህብረት ተቋማዊ ማሻሻያ፣ በኢትዮጵያ እና በህብረቱ መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከርን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
አምባሳደር ሂሩት÷ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትን እንቅስቃሴዎች ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት አጠናክራ እንደምትቀጥል መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡