Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደስታ ሌዳሞ በኢትዮጵያ ከጀርመን አምባሳደር ጋር ተወያዩ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በኢትዮጵያ ከጀርመን አምባሳደር ጀንስ ሃንፊልድ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ርዕሰ መስተዳድሩ÷ የክልሉ መንግስት እየተገበረ ስላለው የልማት አቅጣጫና ድጋፍ በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ለአምባሳደሩ አብራርተዋል።

በዚህም ከግብርና ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ፣ ሴቶችና ወጣቶችን ተጠቃሚ ከሚያደርጉ ፕሮጀክቶች አኳያ እንዲሁም ከይርጋዓለም ኢንዱስትሪ ፓርክ ጋር ተያይዞ የቴክኒክና እገዛና የእሴት ሰንሰለት ማመቻቸት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ስለመሆናቸው አንስተዋል።

አምባሳደሩ በበኩላቸው÷ የጀርመን መንግስት በክልሉ በተለያዩ ዘርፎች በተለይም በግብርናው ዘርፍ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ያነሷቸውን ጉዳዮች እንደግብዓት በመጠቀም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፃቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.