የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ያልፈረሙ ሀገራት እንዲፈርሙ ጥሪ ቀረበ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ፍትሐዊ እና እኩል ተጠቃሚነትን የሚያሰፍነውን የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ያልፈረሙ ሀገራት ስምምነቱን እንዲፈርሙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት በተፋሰሱ አባል ሀገራት መካከል የልማት ትብብር የሚያጠናክር መሆኑንም ገልጸዋል።
ፍትሐዊ እና እኩል ተጠቃሚነትን የሚያሰፍነውን የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ያልፈረሙ ሀገራት እንዲፈርሙ ከሲጂቲኤን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል፡፡
ስምምነቱ ወደ ተግባር መግባቱ በናይል ወንዝ ተፋሰስ የውሃ ዲፕሎማሲ ጉዞ ታሪካዊ ስኬት መሆኑንም አንስተዋል።
የናይል የትበብር ማዕቀፍ ስምምነት ከጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ተፈጻሚነት መግባቱ ይታወቃል።