Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ምንዛሪ ግብይትን ለማሳለጥ ድጋፋችን ይቀጥላል- አቶ ማሞ ምህረቱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ግብይት እንዲሳለጥ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የባንኩ ገዥ ማሞ ምህረቱ አረጋገጡ፡፡

አቶ ማሞ በቦሌ የተከፈቱ እና ሥራ የጀመሩ ሁለት የውጭ ምንዛሪ ግብይት ቢሮዎችን በመጎብኘት አበረታትተዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም ቢሮዎቹ ለንግድም ሆነ ለግል ጉዳይ ወደ ውጭ ለሚሄዱ አካላት የሚፈልጉትን የምንዛሪ አይነት በማሟላት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖራቸው ገዥው ተናግረዋል፡፡

የአስመጭ እና ላኪዎችን ፍላጎት የሚያሟላ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት እንዲኖር ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ግብይት እንዲሳለጥ የሚያደርገውን ድጋፍም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.