Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፉ የነጻ ንግድ ቀጣና ትግበራ ኮሚቴ የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣናን እየጎበኘ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በመንግስት ከፍተኛ አመራሮች የተመራው ሀገር አቀፍ የነጻ ንግድ ቀጣና ትግበራ ኮሚቴ የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣናን እየጎበኘ ነው።

ኮሚቴው የድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጣና አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ በመገምገም ነጻ ንግድ ቀጣናው በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ እንዲገባ ለማስቻል ቀጣይ አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል።

ከዚህ ባለፈም ቁልፍ ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን አስዋጽኦ እንዲያደርጉ ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥ ተጠቁሟል፡፡

የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ከሚያስተዳድራቸው ፓርኮች ውስጥ ወደ ነጻ ንግድ ቀጣናነት በማደግ የመጀመሪያው መሆኑ ይታወቃል፡፡

በቀጣናው በማኑፋክቸሪንግ፣ በንግድ፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ ሎጅስቲክስ እና ተያያዥ ዘርፎች የተሰማሩ ኩባንያዎች ሥራ ለመጀመር በተለያየ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

በጉብኝቱ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር እና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።

በቲያ ኑሬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.