Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ የቡና ልማትን ለማስፋፋት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ በማቅረብ የቡና ልማትን ለማስፋፋት ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የድህረ ምርት ባለሙያ አቶ ጌታቸው አዲስ እንዳሉት÷በቡና ተክል እየለማ ከሚገኘው መሬት ከ133 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚሰበሰብ ይጠበቃል፡፡

በክልሉ ለቡና ልማት ተስማሚ የሆነ ከ361 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት እንዳለ በቅርቡ በተደረገ ጥናት መረጋገጡን አመልክተዋል።

ባለፉት ጊዜያት በተደረገ የተቀናጀ ጥረትም 31 ሺህ 433 ሄክታር መሬት በቡና ተክል ማልማት እንደተቻለ ገልፀዋል።

ከለማው መሬት ውስጥ ከ22 ሺህ ሄክታር በሚበልጥ መሬት የተተከለ ቡና ምርት መስጠት እንደጀመረ መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ለዚህም ጥራቱን የጠበቀ የቡና ምርት በመሰብሰብ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ግንዛቤ የማሳደግ ስራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

በክልሉ ለቡና ልማት ተስማሚ በሆኑ 24 ወረዳዎች የቡና ልማት በኩታ ገጠም ተለይቶ የማስፋፋት ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስገንዝበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.