Fana: At a Speed of Life!

በትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

አደጋው በወረዳው መምህር ሀገር ቀበሌ ቦሰቄ ድልድይ በሚባል አካባቢ ዛሬ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ከአዲስ አበባ ወደ አረርቲ ከተማ 445 ኩንታል ዱቄት ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ተሳቢ ተሽከርካሪ በመገልበጡ የደረሰ ነው፡፡

በአደጋውም ሹፌሩንና ረዳቱን ጨምሮ 4 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉና የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ክፍል ሀላፊ ኮማንደር በለጠ ተክለ ስላሴ ተናግረዋል፡፡

በአላዩ ገረመው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.