የአፍሪካ የመከላከያ ሚኒስትሮች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ የመከላከያ ሚኒስትሮች ጉባዔ ተሳታፊዎች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ የአፍሪካ የመከላከያ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች፣ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ያደረጉ ወታደራዊ አታሼዎች፣ ወታደራዊ ተመራማሪዎች፣ የኢትዮጵያ የጸጥታና ደኅንነት ተቋማት አባላት ተሳትፈዋል፡፡
የመከላከያ ሚኒስትሯ አይሻ መሀመድ(ኢ/ር) በጉብኝቱ ወቅት÷ የአፍሪካ የመከላከያ ኃይሎች ትብብር ሰላምና ደኅንነትን በማረጋገጥ እና የበለጸገች አፍሪካን እውን ለማድረግ ለሀገሪቱ የነፃነት ታሪክ ፈር ቀዳጅ የሆነውን የዓድዋ ድል ታሪክ ለወታደራዊ ልዑኩ አስገንዝበዋል፡፡