Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ላስጠለለቻቸው ፍልሰተኞች መሠረታዊ አገልግሎት እየሰጠች ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የተጠለሉ ፍልሰተኞች መሠረታዊ አገልግሎት እያገኙ መሆኑን አምባሳደር ጸጋአብ ክበበው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ አብራሩ፡፡

በጄኔቫ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ጸጋአብ ክበበው በ75ኛው የሥራ አስፈጻሚዎች የድርጅቱ ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡

በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግርም በኢትዮጵያ የሚገኙ ፍልሰተኞች÷ የትምህርት፣ የሕክምና፣ የሥራ፣ የመንቀሳቀስ እና መሰል አገልገሎቶችን እያገኙ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ሀገሪቱ ጥበቃ ለሚሹ ፍልሰተኞች አስፈላጊውን ከላላ እያደረገች እንደምትገኝ ገልጸው÷ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ በርካታ ፍልሰተኞችን በብዛት መቀበሏ ተግዳሮት እንደሆነባት አንስተዋል፡፡

በዚህም ሀገሪቱ የአየር ንብረት ለውጥ ጫናን ለመቋቋም እያከናወነችው ባለው ሥራ አማካኝነት ፍልሰተኞች በሚገኙባቸው እና በተራቆቱ አካባቢዎች በርካታ ችግኞች ተተክለዋል ማለታቸውን በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

በየዓመቱ በሺህዎች የሚቆጠሩ በርካታ ፍልሰተኞችን ለምታስተናግደው ኢትዮጵያ ለጋሽ ሀገራት ፋይናንስን ጨምሮ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.