ዳሸን ባንክ 6 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር አተረፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዳሽን ባንክ ባለአክሲዮኖች 31ኛ መደበኛና 26ኛ አስቸኳይ ጉባዔ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።
የባንኩ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ዱላ መኮንን በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ባለፈው በጀት ዓመት ዳሸን ባንክ የነበሩ ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ የደንበኞቹን ፍላጎት ሟሟላት ችሏል።
የዳሸን ባንክ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ145 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር መድረሱን ተናግረዋል።
ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ ለባንኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ያበረክተው ድርሻ 11ዐ ነጥብ 1 ቢሊየን ብር መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በበኩላቸው፥ የባንኩ አጠቃላይ ሃብት ባለፈው በጀት ዓመት የ27 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ 183 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር መደረሱን ገልፀዋል፡፡
ባንኩ ባለፈው በጀት ዓመት 1 ነጥብ 44 ሚሊየን አዳዲስ ደንበኞችን ማግኘት እንደቻለና ይህም ለባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ዕድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከቱን ገልፀዋል፡፡
ባንኩ በአሁኑ ወቅት ከ6 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉት የገለጹት ዋና ስራ አስፈፃሚው፥ባለፈው በጀት ዓመት 6 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን ተናግረዋል።
በታሪኩ ወ/ሰንበት