Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የግብርና ልማት መተግበር ይገባል- ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካን የምግብ ሉዓላዊነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የግብርና ልማት መተግበር እንደሚገባ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ገለጹ።

የመጀመሪያው የአፍሪካ አንድ ሺህ ወጣቶች የሥርዓተ ምግብና አግሮ-ኢኮሎጂ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሔደ ነው፡፡

በጉባዔው ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ 250 ወጣቶች በአካል እየተሳተፉ ሲሆን÷ ከ2 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ በበይነ መረብ እየተከታተሉ ይገኛሉ።

በጉባዔው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)÷ የአየር ንብረት ለውጥ በተለይም በግብርናው ዘርፍ ላይ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም የአፍሪካን የምግብ ሉዓላዊነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የግብርና ልማት መተግበር ይገባል ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በስንዴ ልማትና የቱሪዝም ልማት ዘርፎች በስፋት እየሰራች መሆኑን ገልጸው÷ ለዘላቂና የተሳካ የግብርና ልማት በጋራ መስራት እንደሚገባ አብራርተዋል።

በአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ጥምረት ዋና ሃላፊ ሚሊዮን በላይ (ዶ/ር)÷ ጉባዔው አፍሪካውያን በጉዳዩ ዙሪያ የሚመካከሩበትን እድል መፍጠርና ከሥርዓተ ምግብ ጋር በተገናኘ ያሉ ፈተናዎችን በመጋፈጥ በጋራ መፍትሄ ለማበጀት ያለመ እንደሆነ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.