Fana: At a Speed of Life!

ቶዮ ሶላር በ7 ቢሊዮን ብር ወጪ በኢትዮጵያ ፋብሪካ ለመክፈት የሚያስችለውን ስምምነት አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ቶዮ ኩባንያ በ7 ቢሊዮን ብር ወጪ የፀሐይ ሀይል ለማምረት የሚያስችለውን ስምምነት ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር ተፈራርሟል፡፡

ኩባንያው በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሶላር ኢነርጂ ማምረቻ ፋብሪካውን መገንባት የሚያስችለውን ፈቃድ ማግኘቱ ነው የተገለፀው፡፡

ፋብሪካው ተገነንብቶ ሲጠናቀቅ በየወሩ ከ15 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የፀሐይ ሀይል ማመንጫ መሳሪያዎችን ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል።

ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ የክህሎት ልማትን እና የውጭ ምንዛሪ አቅምን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል የተባለ ሲሆን በተጨማሪም ከ1 ሺህ በላይ የስራ እድል እንደሚፈጥር ተመላክቷል፡፡

ስምምነቱን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) እና የቶዮ ሶላር ኩባንያ ዋና ስራ አስኪያጅ ሚስተር ሊ ሁዋያንግ መፈረማቸውን የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.