የሉዓላዊነት ዓርማ የሆነውን ሰንደቅ ዓላማ በክብር መጠበቅ እንደሚገባ ተመላከተ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰንደቅ ዓላማችን የሉዓላዊነታችን ዓርማና መገለጫ በመሆኑ አክብረን እንጠብቀዋለን ሲሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አስካል አልቦሮ ገለጹ፡፡
17ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሃሳብ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለያዩ ዞኖች፣ ወረዳዎች እና ከተሞች ተከብሯል፡፡
በአሶሳ ከተማ በተከበረው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት አፈ-ጉባዔዋ÷ ሰንደቅ ዓላማችን የሉዓላዊነታችን ዓርማና መገለጫ በመሆኑ አክብረን እንጠብቀዋለን ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡