Fana: At a Speed of Life!

የሰንደቅ ዓላማ ቀን ሲከበር አንድነትን በማጎልበት ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከብር አንድነትን በማጎልበት ሊሆን ይገባል ሲሉ የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ሱልጣን አብዱሰላም አስገነዘቡ፡፡

በክልሉ 17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሐሳብ ተከብሯል፡፡

አፈ-ጌባዔው በአከባበሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከብር አንድነትን እና ልማትን ይበልጥ በማጎልበት ሊሆን ይገባል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ጠንክረን በመሥራት ድህነትን ታሪክ በማድረግ ሰንደቅ ዓላማችን በዓለም ከፍ ብሎ እንዲታይ በማድረግ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.