የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት ትርጉም …
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በመላ ሀገሪቱ 17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከብሮ ይውላል፡፡
ለመሆኑ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት እና በሰንደቅ ዓላው መሀል ላይ የሚገኘው ዓርማ ትርጉም ምንድን ነው?
1. አረንጓዴው ቀለም፡- የሥራ፣ የልምላሜና የዕድገት ምልክት ነው፡፡
2. ቢጫው፡- የተስፋ፣ የፍትሕና የእኩልነት ምልክት ነው፡፡
3. ቀዩ ለነፃነትና ለእኩልነት መስፈን የሚደረግ የመስዋዕትነትና የጀግንነት ምልክት ነው፡፡
እንዲሁም በሰንደቅ ዓላማው መሀል ላይ የሚገኘው ዓርማ ትርጉም ከታች የቀረበው መሆኑ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
1. ክብ የሆነው ሰማያዊ መደብ ሰላምን ያመለክታል፡፡
2. ቀጥታና እኩል የሆኑት መስመሮች፡- የብሔሮች፣ የብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንዲሁም የሐይማኖቶችን እኩልነት ያመለክታሉ፡፡
3. ቀጥታና እኩል ከሆኑት መስመሮች የተዋቀረው ኮከብ፡- የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በመፈቃቀድ የመሠረቱትን አንድነት ያመላክታል፡፡
4. ቢጫ ጨረር፡- በመፈቃቀድ አንድነት ለመሰረቱት ብሔር፣ ብሔረሰቦች የፈነጠቀውን ብሩህ ተስፋ ይጠቁማል፡፡