Fana: At a Speed of Life!

የክልሉ ምክር ቤት የ2017 የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም መገምገም ጀምረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አስተዳደር ምክር ቤት የ2017 በጀት ዓመት የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን መገምገም  ጀምሯል።

ምክር ቤቱ በተያዘው የ2017 በጀት ዓመት ያለፉት ሦስት ወራት የዕቅዶችን አፈጻጸም በመገምገም ጥንካሬዎችን ፣ ውስንነቶችን እና ትምህርት የሚወሰድባቸው ጉዳዮችን እንደሚለይ ተገልጿል፡፡

በመድረኩ የሁሉም ሴክተሮች ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ተግባሩ የተመራበት መንገድና የተገኙ ውጤቶች ተለይተው ቀጣይ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ ይጠበቃል መባሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.