Fana: At a Speed of Life!

አይ አር ሲ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚያጠናክር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በዓለም አቀፉ ነፍስ አድን ኮሚቴ (አይ አር ሲ) ካንትሪ ዳይሬክተር ፓውሎ ሲሙስቺ ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ጤና ሚኒስቴር በአደጋ ምላሽ አሰጣጥ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በቅርበት በመስራት ለድንገተኛ አደጋዎች የሚሰጠውን ምላሽ ማሳለጥ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

ዶ/ር መቅደስ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች በመረጃ ላይ የተመሰረተ ድጋፍ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጠቁመው÷የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡

አጋር ድርጅቶች ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎችና በድንበር አካባቢ ክትባትን ተደራሽ ለማድረግ ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል፡፡

ፓውሎ ሲሙስቺ በበኩላቸው÷ተቋማቸው ድንገተኛ አደጋ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ እንደሀገር ቅድሚያ የሰጠቻቸው የጤና ጉዳዮች ላይ ከአጋር ድርጅቶች ጋር ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ መናገራቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.