ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር) በአረካ ከተማ አቅራቢያ የሚገነባውን የአውሮፕላን ማረፊያ ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል የፖለቲካና ርዕዮተ-ዓለም ዘርፍ ኃላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር) በወላይታ ሶዶ ከተማ አረካ አቅራቢያ የሚገነባውን የአውሮፕላን ማረፊያ ጎበኙ፡፡
በጉብኝታቸውም ለአውሮፕላን ማረፊያው ግንባታ ሲባል ከአካባቢው የሚነሱ የልማት ተነሺዎችን እና የመንገድ ከፈታ ሥራን ጨምሮ ሌሎች ቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ተመልክተዋል፡፡
ለአውሮፕላን ማረፊያው ግንባታ ሥራ ሲባል ለልማት ተነሺዎች የካሳ ክፍያ መፈጸሙና ከአካባቢው እንዲነሱ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ ነው መባሉን የወላይታ ሶዶ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
በ120 ሔክታር መሬት ላይ የሚያርፈው የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ሲጠናቀቅም ለአካባቢው ዕድገት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡
ግንባታው ያለምንም መስተጓጎል በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የሚያስችሉ ተግባራት እተከናወኑ ነው ተብሏል፡፡