5ኛው ብሔራዊ የሳይበር ደኅንነት ወር መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አምስተኛው ብሔራዊ የሳይበር ደኅንነት ወር በሳይንስ ሙዚየም መካሄድ ጀመሯል።
የሳይበር ደኅንነት ወሩ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ “የቁልፍ መሠረተ ልማት ደኅንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ሐሳብ ነው የሚካሄደው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምኅረቱ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ፣ የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመርሐ-ግብሩ ላይ መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የሳይበር ደኅንነት ወር እንደ ሀገር ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን÷ ወሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘንድሮ ለ21ኛ ጊዜ ነው የሚከበረው።
በሳይበር ደኅንነት ወር ላይ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ-ግብሮች እንደሚካሄዱም ተጠቁሟል።