5ኛው የሳይበር ደኅንነት ወር በሳይንስ ሙዚየም ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፉ የሳይበር ደኅንነት ወር “የቁልፍ መሠረተ-ልማት ደኅንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ሐሳብ ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ወር እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡
የሳይበር ደኅንነት ወርን ማካሄድ ያስፈለገው ተቋማትና ዜጎች በዘርፉ ያላቸውን ንቃተ-ህሊና ለማሳደግ ነው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ደረጃ ውጤታማ የሆነ ቅንጅት በመፍጠር የሳይበር ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የወሩ መከበር እግዛ እንደሚያደርግም ተገልጿል፡፡
ወሩ ሲከበር በዘርፉ የሚደረጉ ውይይቶችና ምክክሮች፣ የተማሪዎች ውድድሮች፣ የ5 ሚሊየን የኮደርስ ኢኒሼቲቭ ለሳይበር ደኅንነት የሚጫወተው ሚና በሚል የሚዘጋጁ ፕሮግራሞች እንደሚኖሩም ተመላክቷል፡፡