Fana: At a Speed of Life!

ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለማጠናከር እንደምትሰራ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ አዲስ ከተሾሙት በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር የንስ ሃንፌት ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ምስጋኑ÷ ኢትዮጵያ እየተገበረችው ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ብሔራዊ ምክክርና የሽግግር ፍትሕ ሂደቶችን እንዲሁም በሌሎች የልማት ሥራዎች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።

ኢትዮጵያ ለቀጣው ሰላም፣ ደኀንነትና ልማት ያላትን ቁርጠኝነት አጠናክራ እንደምትቀጥልም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮ-ጀርመንን የረጅም ጊዜ ግንኙነትን በኢኮኖሚያዊ ትብብር የበለጠ በማጠናከር የጋራ ተጠቃሚነትን ማስፋት እንደሚገባ አንስተዋል ።

አምባሳደር የንስ ሃንፌት በበኩላቸው ÷ኢትዮጵያ እየተገበረችው ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ፣የብሔራዊ ምክክርና የሽግግር ፍትሕ እንቅስቃሴ አድንቀዋል፡፡

እንዲሁም ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት እየተጫወተች ያለውን ሚና እና አሸባሪው አልሸባብን በመዋጋት ረገድ ላበረከተችው አስተዋጽኦ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

የሀገራቱን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በፖለቲካው ዘርፍ ብቻ ሳይሆን በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ያላቸውን ቁርጠኝነት መግለጻቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.