ፍሎሪዳ ሀሪኬን ሚልተን በተሰኘው ውሽንፍር ያዘለ አውሎ ነፋስ መመታቷ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የፍሎሪዳ ግዛት ሀሪኬን ሚልተን በተሰኘው ውሽንፍር ያዘለ አውሎ ነፋስ ክፉኛ መመታቷ ተገለጸ፡፡
በአደጋው የመሬት መንሸራተት፣ ጎርፍ እና ነጎድጓዳማ የዝናብ ሁኔታ መከሰቱም ተገልጿል።
በአደጋው ከሁለት ሚሊየን በላይ ቤቶች እና የቢዝነስ ተቋማት የሀይል መቋረጥ ያጋጠማቸው ሲሆን ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ስለመኖራቸውም እየተነገረ ይገኛል።
የአሜሪካ ብሔራዊ የአደጋ ምላሽ ሃላፊ ዲን ክሪስዌል፤ መንግስት የሰጠውን የአደጋ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ እስካሁን ከ31 ሀገራት የተወጣጡ ከ70 ሺህ በላይ የፍሎሪዳ ነዋሪዎች በጊዜያዊ መጠለያዎች ይገኛሉ ብለዋል፡፡
በፍሎሪዳ የተከሰተው ሚልተን ሀሪኬን እየቀነሰ ቢሆንም አሁንም ተጨማሪ የአደጋው ስጋት መኖሩ ጠቁመዋል።
ሚልተን ሀሪኬን ዝቅተኛ ግምት ከሚሰጣቸው ዝናብ ያዘሉ አውሎ ነፋሶች አንዱ ቢሆንም በቅርቡ ግን አስፈሪ እና ከፍተኛ አደጋዎችን የሚያስከትል ክስተት ውስጥ መመደቡን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡