ማዕከሉ በጥምር ግብርና ምርቶች ሥራ ላይ በስፋት መሠማራቱን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦላይ ከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ማዕከል ከተጣለበት ዋና ኃላፊነት ጎን ለጎን ለሰራዊቱ ለምግብነት የሚውሉ የጥምር ግብርና ውጤቶችን እያመረተ መሆኑን አስታወቀ፡፡
በዚህም ከ87 ሄክታር በላይ በቆሎ በክላስተር መልማቱን የገለፁት የማዕከሉ አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ጡምሲዶ ፊጣሞ÷ በእንስሳት እርባታ፣ በንብ ማነብ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በልዩ ልዩ የግብርና ስራዎች መሠማራታቸውን አብራርተዋል፡፡
በዚህም ከጥምር ግብርናው የተገኙ ውጤቶችን ለሰራዊቱ ምግብ አድርጎ ከማቅረብ ባለፈ ለሰራዊቱ ቤተሰቦች በቅናሽ ዋጋ እየቀረበ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ሰራዊት ከማሰልጠንና ከማብቃት ባለፈ ለሰራዊቱ የምናወጣውን በጀት ለማገዝ የሚያስችል የተለያዩ ምርቶችን እያመረትን ነው ብለዋል፡፡
እንዲሁም ለፈርኒቸር ምርቶች ማዕከሉ ያወጣው የነበረውን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ብር ማዳን መቻሉንም ገልጸዋል፡፡
በዓለምሰገድ አሳዬ