Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎችን እንደሚደግፍ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የግብርና ቁመና ምን እንደሚመስል በኢትዮጵያ ለዓለም የምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዝላታን ሚሊሲክ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም የኢትዮጵያ ግብርና ለአጠቃላይ ዕድገት፣ ለወጪ ንግድ እንዲሁም የገቢ ምንጭ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።

25 ከመቶ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ሜካናይዜሽን እንደሚጠቀሙ ጠቅሰው፤ ባለፉት ስድስት ዓመታት 11 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በኩታ-ገጠም መልማቱን ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ 95 ከመቶ አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ስለሆኑ የእነዚህን አርሶ አደሮች ሕይወት ለመቀየር የዓለም ምግብ ፕሮግራም ሰፊ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

ዝላታን ሚሊሲክ በበኩላቸው፤ ተቋማቸው በምግብ ዋስትና በኩል የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ምሰሶ የሆነው ግብርና እመርታ እያሳየ ነው በማለት ገልጸው፤ በመስኖ ልማትና በሌሎች ዘርፎች እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አድንቀው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

በእህል ጎተራ ስራ፣ በእሴት መጨመር፣ በድህረ ምርት አያያዝ፣ በግብርና ኢንሹራንስ በቴክኖሎጂ የመደገፍ ስራዎችን በጋራ እንሰራለን ማለታቸውን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.